**እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!...

10.1 Million ETB
@housinginaddisababa
TypeFor Sale
Location@housinginaddisababa

**እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን! ኢትዮ ቴሌኮም ባለአክሲዮኖቹ አክሲዮናቸውን በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ መሸጥ፣ መግዛት እና ማስተላለፍ እንደሚችሉ በታላቅ ደስታ ያበስራል!** በዛሬው ዕለት የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፤ ኩባንያው አስፈላጊ ሕጋዊ አሠራሮችን በማሟላት ባለአክሲዮኖች በሁለተኛ ገበያ (ESX) አክሲዮኖችን መግዛት፣ መሸጥና ማስተላለፍ እንዲጀምሩ ዝግጁ ማድረጉን በይፋ አብስረዋል። በተለይም ባለፉት ወራት በተከናወነ መጠነ-ሰፊ የማጣራት ሥራ ከ47,377 ባለአክሲዮኖች ውስጥ 45,366ቱ (95.8 በመቶ) ምዝገባቸውን በስኬት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። ይህም በገንዘብ ሲሰላ 3.04 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው 10.1 ሚሊዮን አክሲዮኖች ለግብይት ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል ብለዋል። በዕለቱ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተዋናዮች በተገኙበት የአክሲዮን ግብይት ማስጀመሪያ የደወል ሥነ ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ግብይትም በሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያው በይፋ ተከናውኗል። ባለአክሲዮኖች አክሲዮናቸውን ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ከተሰጣቸው አገበያዮች ወይም የኢንቨስትመንት ባንኮች ዘንድ በመቅረብ የንግድ አካውንት መክፈት ይኖርባቸዋል። በመጪው በጀት ዓመት የፋይናንስ ኦዲቱ እንደተጠናቀቀ በሚጠራው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ (AGM) ላይ የትርፍ ክፍፍል መጠን ተወስኖ ይፋ ይደረጋል። የባለቤትነት ድርሻቸውን ሂደት ያጠናቀቁ ባለአክሲዮኖች፤ የባለቤትነት መብታቸው ከያዝነው በጀት ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የሚጠበቅላቸው ይሆናል። ለተጨማሪ መረጃ፦ https://bit.ly/4nROnuL

Contact: TBD
Open in search view →