የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ...
See Description
@housinginaddisababa
TypeFor Sale
Location@housinginaddisababa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ ********** የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት አካሄደ። ካቢኔው በዛሬው ስብሰባው በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ በዚህ መሰረት፡- 1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሻሻለ የፋይናንስ አስተዳደር ይበልጥ ለማዘመን፣ ተጠያቂነትንና የአሰራር ግልፀኝን ለማጐልበት በተዘጋጀዉ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል። 2ኛ. በከተማዉ እየተገነባ ያለዉን ሰፊ የቤት ልማት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረዉ፣ የቤቶች ኮርፖሬሽን ሪፎርም በማጠናከር እና የማስፈፀም ብቃት ለማሳደግ በተዘጋጀዉን ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል። 3ኛ. የመሬት ማስፋፍያ ለጠየቁ ተኪ ምርት ለሚያመርቱ ኢዱስትሪዎች፣ ለወጣቱ የስራ ዕድል የፈጠሩ ፕሮጀክቶች፣ ሆቴሎች እንዲሁም፥ በከተማ አስተዳደሩ ከሐይማኖት ተቋማት ጋር በተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት የሚያስችል መሬት በምደባ ለማስተላለፍ የቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ፣ ተፈፃሚ እንዲሆን አድፅድቋል።
Contact: TBD
Open in search view →