የሽያጭ ውል ጊዜ ገደብ የተራዘመ መሆኑን ለማሳወቅ የቀረበ ማስታወቂያ...
See Description
@housinginaddisababa
TypeFor Sale
Location@housinginaddisababa
የሽያጭ ውል ጊዜ ገደብ የተራዘመ መሆኑን ለማሳወቅ የቀረበ ማስታወቂያ ተቋማችን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ህንጻ ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን እና በካፒታል ፕሮጀክት የተገነቡ ንግድ ቤቶችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ 8ኛ ዙር እና 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ በተመሳሳይ ቀን በአንድ የጨረታ ሰነድ ማውጣቱ እና የጨረታው 1ኛ ደረጃ አሸናፊዎች ግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) እስከ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም የሽያጭ ውል ስናከናውን መቆየታችን ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከሲስተም መቆራረጥ እና ተጫራቾች ካነሱት ከባንክ የገንዘብ ዝውውር መዘግየት አንፃር የባከኑ የስራ ቀናትን ታሳቢ በማድረግ ለተጨማሪ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከግንቦት 25 እስከ ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ በመሆኑ ቀደም ሲል በተገለፀላችሁ የመዋዋያ ቦታ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ በኩል የሚጠበቅባችሁን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት በተገለጸው የሽያጭ ውል ጊዜ ገደብ ውስጥ ውል መፈጸም እንድትችሉ ጥሪ የቀረበላችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
Contact: TBD
Open in search view →